ሀ/ የውርስ አጣሪ መሆን የሚችለው

 

 • ያለኑዛዜ ወራሽ የሆነ ሰው ይህም ልጅ፣ ልጅ ከሌላ ወላጅ፣ወንድም እህት …፣
 • በኑዛዜ ጠቅላላው የሟች ንብረት እንዲወርስ ኑዛዜ የተደረገለት ሰው፣
 • አካለመጠን ያልደረሱ ወይም በህግ የተከለከሉ ህጋዊ ወራሾች ሞግዚት፣
 • በወራሾች ስምምነት የሚመረጥ ሰው፣
 • ወራሾች ስምምነት የሚመረጥ ሰው፣
 • ወራሾች ካልተስማው በፍ/ቤት የሚመረጥ ውርስ አጣሪ፣
 • በኑዛዜ የሚመረጥ የውርስ አጣሪ ነው፡፡

ለ/ የውርስ ማጣራት ማለት

 1. የውርስ ተቀባይ እነማን እንደሆኑ መወሠን፣
 2. የውርስ ሀብት ምን መሆኑን ማጣራት፣
 3. ለውርስ የሚከፈለውን ገንዘብ መቀበል ለመክፈለል አስገዳጅ የሆነውን ዕዳ መክፈል፣
 4. ሟቹ በኑዛዜ ስጦታ ላደረገላቸው ስዎች የሰጣቸውን መክፈል፣

ሐ/ የውርስ አጣሪው ዋና ዋና ሰራዎች

1. ሟቹ አንድ ኑዛዜ ትቶ እንደሆነ መፈለግ

 1. ኑዛዜውን የሟችን ፅሁፎች በመመርመር ከውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት ፣ከንሰሃ አባት/ካለ/ ፣ከፍ/ቤት ፣ወይም የሟቹን ኑዛዜ
 2. ተቀብለዋል ከተባሉ ስዎችና አካላት ብርቱ ጥረት አድርጐ መፈለግ አለበት፡፡
 3. ሟች ኑዛዜ ትቶ ከሆነ ሟቹ በሞት በአርባኛው ቀን ወይም ኑዛዜው የተገኘው ሟቹ ከሞት ከአርባ ቀን በኃላ ከሆነ ኑዛዜው በተገኘ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለወራሾች ይነበብላቸዋል፡፡
 4. የውርስ አጣሪው የሟቹ ኑዛዜ ሲነበብ የሟች ህጋዊ ወራሾች በመሉ እንዲገኙ ማስታወቅ አለበት፣የሚያስታውቀው በአካል በመንገር፣ በአድራሻቸው ደብዳቤ በመፃፍ አስፈላጊም ሲሆን በጋዜጣና በሌሎች ዘዴዎች ሲያሳውቅ ይችላል፡፡
 5. የሟች ኑዛዜ ሲነበብ ቢያንስ አራት አካለመጠን ያደረሱ ሰዎች መገኘት አለባቸው፡፡
 6. የውርስ አጣሪውና ሌሎች ወራሻች ኑዛዜው ፎርማሊቲውን ያሟላና ዋጋ ያለው ፣ፈራሽ ያልሆነ መሆኑን ይመረምራሉ፡፡
 7. ኑዛዜው በውርስ አጣሪውና በወራሾች ተቀባይነት ካገኘ ለኑዛዜ ወራሽ ለሆነው ሰው መክፈል፣
 8. ኑዛዜውን በመቃወም የሚቀርብ አቤቱታ ኑዛዜው ከተነበበ በ15 ቀን ውስጥ መቅረብ አለበት፡፡

 2. ወራሾች እነማን እንደሆኑ መለየት እዚህ ላይ የሟች ያለኑዛዜና የኑዛዜ ወራሾችን

     እክሌ እከሌ ብሎ በተራ ቁጥር መስቀመጥ ሊሆን ይችላል፡፡

 3.  የውርስ ሀብት ማስተዳደር፣

1. ቢቻል ሟቹ በሞተ በአርባ ቀን ውሰጥ የሟቹን አጠቃላይ ንብረቶች በመዝገብ መዝግቦ መያዝ፣

2. አዳዲስ ንብረቶች ሲገኙም በተገኙ በ1ዐ ቀን ውስጥ በመዝገብ ውስጥ እንዲገብ ማድረግ፣

3. በሟቹ እያንዳንዱ ሀብቶች ላይ ለጊዜው የዋጋ ግምታቸውን ማስቀመጥ ይህ ከወራሻች ጋር በመስማማት ሲያደርገው ይችላል፡፡

4. የውርሱ ንብረቶች እንዲጠበቁ እስፈላጊ ነገሮች ሁሉ ማድረግ፣

4. መክፈያቸው የደረሰውን የውርስ ሀብቶች መቀበል እዳዎችን መክፈል፣

1. ሟች ያበደረው ሰው ካለ ብድሩን የመክፈያ ግዜ ደርሶ ከሆነ መቀበል፣

2. ሟች የተበደረው ዕዳ ካለና የመክፈያ ጊዜው ደርሶ ከሆነ መክፈል፣

3. የሟች አበዳሪዎች ተበዳሪያቸውን መሞቱን አውቀው መብታቸውን እንዲጠየቁ አስፈላጊ የሆነ ማስታወቂያዎችን  ማውጣት የማስተወቂያ መውጣት ፊደል ሐ/1/ ስር እንደተጠበቀሰው ሊሆን ይችላል፡፡

5   ሟች በኑዛዜው ያደረጋቸውን ሰጦታዎች ኑዛዜው ተቀባይነት ያገኘ ከሆነ መክፈልና የሟች ኑዛዜ እንዲፀም አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ

6   ሟች ኑዛዜ ያልተወ ከሆነ የሟች ያለኑዛዜ ወራሾችን በመለየት የኑዛዜውን ድልድል እንዲት እንደሆነ ለወራሾች ማሣወቅ፡፡

1. እያንዳንዱ ወራሽ ምን እና ምን ያህል ሊውርስ እንደሚችል ማሣውቅ፣

2. የንብረቶችን ግምትና የሚወረሱ ንብረቶችን ዝርዝር ማሣወቅ፣

3. የውርስ አጣሪው ባቀረበው የአከፋፈል አይነት የማይሰማማ ለፍ/ቤቱ እቤቱታ መቅረብ ይችላል፡፡

7   ሌሎች ስራዎችን ከፍ/ብ/ህ/ ቁጥር 946-1125 ድረስ ያሉትን እንደ አግባብነታቸው መሠረት ነው፡፡

 

 
ተጨማሪ ጥያቄ አስተያየት ቢኖርዎት ያነጋግሩን፡፡fikadu@ethiopianlaw.com

 አግባብነት ያላቸው ተጨማሪ ህግ መረጃዎች ከማናቸውም ኢትዮጵያዊ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የፍቺ ጠበቃ፣ኢትዮጵያዊ የቤተሰብ ጠበቃ… ማግኘት ይችላሉ፡፡