የገቢ ግብር ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ የገቢ ግብር አዋጅ 286/1994 የሚያስቀምጣቸውን መረጃዎች ከዚህ እንደሚከተለው እንካፍልዎት፡፡ በአንቀፅ 87 መሠረት ማንኛውም ግብር ከፋይ በገቢ ማስታወቂያው ላይ ሊከፍል የሚገባውን ግብር አሣንሶ ያስታወቀ እንደሆነ ያሣነሠውን ግብር መጠን 1ዐ% (አስር በመቶ ) ወይም በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 እንደተመለከተው የተቀነሠው ገቢ ከፍተኛ የሆነ እንደሆነ አሣንሶ ያስታወቀውን ግብር ሀምሣ በመቶ (5ዐ%) መቀጫ ይከፍላል፡፡ አሣንሶ ያስታወቀው ግብር ከፍተኛ ነው ሊባል የሚችለው መቼ ነው ለሚለው ጥያቅ አንቀጽ 87/2/ መልስ ይሰጣል፡፡ በዚሁ አንቀጽ መሰረትም አንድ ግብር ከፋይ ያስታወቀው /የከፈለው/ ግብር አሳንሶ ነው የሚባለው ከዚህ በታች ከተመለከቱት ከአነስተኛው የበለጠ እንደሆነ ነው፡፡

  1. በገቢ ማስታወቂያ መታየት ካለበት ግብር 25% /ሀያ አምስት በመቶ/ ወይም
  2. በገንዘብ ደረጃ 20,0000.00 (ሀያ ሺ ብር)

ግብር ከፋዩ ይግባኝ ያቀረበ ቢሆንም ይግባኙን የሚመረምረው የይግባኝ ሠሚ ጉባኤ ወይም ፍርድ ቤት የመጨረሻውን ውሣኔ እሰከሚሠጥ ድረስ የመቀጫው ተፈፃሚነት ይቀጥላል፡፡

 

ተጨማሪ አስተያየት ወይም ጥያቄ ካለዎት ያግኙን

አግባብነት ያላቸው ተጨማሪ ህግ መረጃዎች ከማናቸውም ኢትዮጵያዊ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ ታክስ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የቤተሰብ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የወንጀል ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የንብረት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የካሳ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የንግድ ምልክት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የኢሚግሬሽን ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የፓተንት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የኮፒራይት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የስራ ፈቃድ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ ጠበቃ … ማግኘት ይችላሉ፡፡