የገቢ ግብር ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ የገቢ ግብር አዋጅ 286/1994 የሚያስቀምጣቸውን መረጃዎች ከዚህ እንደሚከተለው እንካፍልዎት፡፡ በአዋጁ አንቀጽ 91 ላይ እንደተደነገገው ግብር ከፋዩ ከተከፋይ ሂሣብ ላይ ግብር ቀንሶ ለሚያስቀረው ሠው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን ያላቀረበ እንደሆነ ግብር ቀንሶ የሚያስቀረው ሠው ከተከፋዩ ሂሣብ ላይ 3ዐ% ቀንሶ ገቢ ያደርጋል፡፡

ከተከፋይ ሂሣብ ላይ ግብሩን ቀንሶ ገቢ ማድረግ ለሚገባው ሠው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን ያላቀረበ ግብር ከፋይ ከላይ ከተገለፀው በተጨማሪ 5ዐዐዐ.00 ብር ወይም ሊከፈለው የሚገባውን ሂሣብ ከሁለቱ አነሰተኛውን በመቀጫ መልክ ለግብር አስገቢው ባለስልጣን እንዲከፍል ይደረጋል፡፡

ተጨማሪ አስተያየት ወይም ጥያቄ ካለዎት ያግኙን

አግባብነት ያላቸው ተጨማሪ ህግ መረጃዎች ከማናቸውም ኢትዮጵያዊ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ ታክስ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የቤተሰብ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የወንጀል ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የንብረት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የካሳ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የንግድ ምልክት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የኢሚግሬሽን ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የፓተንት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የኮፒራይት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የስራ ፈቃድ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ ጠበቃ … ማግኘት ይችላሉ፡፡