በህገ መንግስቱ የግል ሕይወት የማክበርና የመጠበቅ በአጠቃቀሙ እንደመርህ /principle/ የማይገድብ አድርጐ ቢያስቀምጣቸውም በልዩ አስተያየት / exception / የተቀመጠው የግል ሕይወት የመጠበቅ እና የመከበር መብት ሰፊ እና አብዛኛውን ጊዜ ለትርጉም የተጋለጡ እንዲሁም አሻሚ በመሆናችው ያልተገደቡ ናቸው ለማለት አያስደፍርም  ምክንያቱም በህግ  መንግስቱ አንቀፅ 26/3/ የመንግስት ባለስልጣኖች የማስከበር እና የማክበር ግዴታ አለባቸው ይልና የሚገደቡበትን ሁኔታ በጥቅሉ አስቀምጧል፡፡ እነሱም አስገዳጅ ሁኔታ ሲፈጠሩ በብሔራዊ ደህንነትን የሕዝብን ሰላም ወንጀልን ለመከላከል ጤናንና የሕዝብን የሞራል ሁኔታ በመጠበቅ ወይም የሌሎችን ግለሰቦች መብትና ነፃነት በማስከበር ላይ በተመሰረቱ ዝርዝር ሕጎች መሠረት እንደሆነ ይዘረዝርልናል፡፡ ስለዚህ ይህ የግል ሕይወት የመከበርና የመጠበቅ መብት በተለያዩ ህጐች እና ደንቦች ሊገደቡ እንደሚችሉ ከህገ መንግስት አንቀፅ 26/3/ መረዳት እንችላለን፡፡

የሰው ምስል እና የፍትሀብሔር ህግ

በፍታብሔር ህጉም ላይ ስንመጣ በተለይም የሰው ስዕል በተመለከተ በአንቀፅ 27 እንደመርህ /ቅቈሽቃስሽቅቁስ/ ባለ ፎቶ ግራፋ ወይንም ባለስዕሉ ካልፈቀደ በቀር የማንኛውም ሰው ፎቶ ግራፍ /ሰዕል በህዝብ አደባባይ ሊለጠፍም ሆነ ሊባዛ ወይንም ሊሸጥ አይችልም፡፡ይል እና በአንቀጽ 28 በልዩ አስተያየት /exception/ ሰፋ ያለ እና ለትርጉም የተጋለጠ ጥቅል ሀኔታዎች አስቀመጧል፡፡ የነዚህንም በአንቀጽ 28  በልዩ አስተያየት /exception/ በሆኑት የትርጉም አሻሚነታችውን ለአብነትም አንዳንዱን ብንመለከት በሰፊው አከራካሪ ነጥብ እናገኛለን፡፡

በአንቀጽ 28 ልዩ አስተያየት

የፎቶግራፍ ወይም የስዕል መባዛት ምክንያት የሆነው ባለፎቶግራፋ የታወቀ ሰው በመሆኑ ወይም ሕዝባዊ ሥራ ምክንያት ወይም በፍርድና በፖሊስ መሥሪያ ቤቶች በኩል አስፊላጊነቱ የተረጋገጠ ምክንያት ያለው በመሆኑ ወይም ለኪነ ጥበብ /ሲያንስ/ለሥልጣኔ አስተዳደግ ወይም ለትምህርት መስጫ ጥቅም በመሆኑ ወይም ደግሞ የፎቶግራፋ መባዛት የተፈጸመ ሥርዓት ጋር ግንኙነት ባለው ምክንያት ሲሆን የባለፎቶግራፋ ፈቃድ አስፈላጊ አይደለም፡፡

የታወቀ ሰው

1. “የስዕሉ ወይንም የባለ ፎቶ ግራፍ መባዛት ምክንያት የሆነው ባለ ፎቶ ግራፍ “የታወቆ ሰው” በመሆኑ ”የሚለውን ሀረግ ብንውስድ አንድ ሰው የታወቀነው ሊባል የሚችለው በምን ያህል ሰው ሊታወቅ ሲችል ነው ወይስ ይህ የተወቀ ሰው ሊባል የሚችለው በባለስልጣን መስራያ ቤት እውቅናው ሲረጋገጥ /official statement/ ሲገኝ ነው፡፡ ይህም በመሆኑም የአንድ ስው ታዋቂ ነው ወይንም አይደለም የሚለውን ለመወሰን ትክክለኛ መስፈርት ማግኘት አይቻልም፡፡ ስለዚህ ለምሣሌ የአንድ ሰው ፎቶ ግራፍ አትሞ ይህ ሰው በዚህ መረጃ በዚህ ቀበሌ የታወቀ ደንበኛ አናጢ ሰው ነው በማለት የምስሉን ህትምት ማሰራጨት ይቻላል ማለት ነው፡፡

ለኪነ ጥበብና /ሳይንስ/ጥቅም

2. ለኪነ ጥበብና /ሳይንስ/ ጥቅም የሚለውን ብንመለከት ይህ የልዩ አስተያየት /ለቦስስቅቋሽቄቃ/ በእጅጉ ለትርጉም የተጋለጠ ነው ምክንያቱም ኪነጥበብ በኪነጥበብ ሣይንሰም እንደሚታወቀው ኪነጥበብ/ Art / እጅግ ሰፊ ጥቅም ያለው ከፈጠራ ጋር የተገናኘ በመሆኑ አንድ ሠው የአንድ ግለስብ ፎቶ ግራፍ/ምስል/ የተወሰነ ፈጠራ አክሎበት ለምሣሌ የሰውየውን ምስል የትዝታ ስሜትን ይገልጣል ብሎ ቢያሣትመው እንዲሁም በተመሣሣይም የአንድ ሰው ምስል ፎቶግራፍ ከተፈጥሮ ጋር በማቀናበር ለምሣሌ የአንድን ሰው ፎቶ ግራፍ በቅጠል ወይም በውሃ ላይ እንዳለ አስመስሎ በማቀናበር የተለየ ትርጉም በመሰጠት የፈጠራ ሰራ/ኪነጥበብ ነው/ በማለት የአንድ ሰው ምስል ማተም ወይም ማባዛት ሊቻል ይችላል፡፡

3. ለስልጣኔ አስተዳዳግ የሚለውን ቃል ብወስድ ይህ በሰልጣኔ አስተዳደግ ጥቅም የሚለውን የቃሉን ትርጉም ብንመለከት የሰልጣኔ እድገት ሊባል የሚችልን ለምሣሌ የኢኮኖሚ፣የባሕል፣ የማህበራዊ፣ የፖለቲካ ሰልጣኔ እና እድገት ሊሆን ይችላል በመሆኑም የባህል ስልጣኔን ወስደን የአንድን ሰው ፎቶ ግራፍ ባለባበሱ ወይንም በፀጉር አቆራረጡ በመሣሰሉት የሰልጣኔ እድገትን ያሣያል በማለት እንደሞዴሊስት አድርጐ ፎቶውን አባዝቶ ማሣየት ይቻላል፡፡

4. ለትምህርት መስጫ ጥቅም፣ ይህንን ሀረግ ብንመለከት እንደሚተወቀው ሁሉ ለትምህርት መስጫ ወይንም ለማስተማሪያ የሚሆኑ ነገሮች በጣም ሰፊና እንደተመልካቹ ወይንም እንደተማሪው እይታ እና አሰተሣስብ የሚለያይ ጉዳይ ነው፡፡ በመሆኑ እንበልና አንድ የታሪክ ሙሁር የአንድ ደንዳና ዘለግ ያለ ቁመና ያለው የሆነን ሰው ምስል ጥንት በድንጋይ ዘመን የሚኖሩ ሰዎችን ይመስላል ስለዚህ የስዎችን አካላዊ ገፅታን ላንባቢዎች በቀላሉ ያሰረዳልኛል ብሉ ሊያሣትም ካሰበው የድንጋይ ዘመን ጥናታዊ ፅሁፍ ጋር አብሮ ሊያሳትመው ይችላል፡፡

ካሳ እና ቅጣት

በቅጂ መብት አዋጅ ላይ ቅጂን በታመለከተ በጥፋተኛ ላይ የሚሰጡት ቅጣት በአይነት ሁለት ሲሆኑ የመጀመሪያ የፍትሀብሔር መፍትሄ ሲሆን ሁለተኛው የወንጀልኝነት ቅጣት ነው፡፡

የፍትሀብሔር መፍትሄ

በጥቅሉ ለአንድ የቅጅ መብተን የተላለፈ ሰው የሚሰጠሙ ፍትሀብሔራዊ ፍርድ ያለአግባብ የበለፀገበትን ለባለ ቅጅው እንዲክስ እና የባለ ቅጅው ውጭና ኪሣራ የቅጂን መብት የጣሰው ሰው ወይንም አካል እንዲከፍል ይደረጋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በፍትሀብሔር መፍትሂ ላይ የአስቀመጠው አንድ የቅጂ መብትን የጣስ ሰው ሊሸፈን የማይችል ሲሆን 1ዐዐ,ዐዐዐ /አንድ መቶ ሺ/ ለባለ ቅጅው የሞራል ካሣ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡

የወንጀል ቅጣት

የወንጀል ህጐ የበለጠ ቅጣት የማያሰቀጣ ከሆነ በቅጂ መብት አዋጅ ላይ ያሉትን የቅጅ ባለቤትን መብት ሆነ ብሎ የጣሰ ማንኛውም ሰው በ5 ዓመት በማያንስ እና 1ዐ ዓመት በማይበለጥ ፅኑ እሰራት ይቀጣል፡፡

እንዲሁም የቅጂ መብት የጣስ ሰው በቸልተኝነት ሲሆን ከ1-5 ዓመት በማያንስ ይቀጣል፡፡ ከዚህ ጋር ከወንጀል ቅጣት አብሮ መያዝ፣ መውረስ እና ማስወገድን ያካትታል፡፡

 ማጠቃለያ

በጥቅሉ በኢትዮጵያ ህግ የግል ህይወትን የማክበርና የመጠበቅ መብት እንደ መርህ አጠቃቀማቸው ሊገደብ የማይችል ነው ተብሉ በህገ መንግስቱ እንዲሁም በፍትሀብሔር ህግ ውስጥ ቢቀመጡም በተለየ አስተያየት/ exception / ይህን በአጠቃቀሙ ያልተገደቡ ያላቸውን መብቶች በሰፊው ለትርጉም እንዲጋለጡ በመተው የአንድ ሠው የግል ህይወት /privacy / የጠበበ እንዲሆን አድርጐታል፡፡

 በያዝነው ጉዳይ ላይ ስንመለስ የአንድ ሰው ስዕል ያለግለሰቡ ፈቃድ በህዝብ አደባባይ መለጠፋ ወይንም የተከለከለ መሆኑን ቢሆንም ያለ ፍቃዱ መባዛቱን ወይንም በህዝብ አደባባይ ላይ መለጠፋን ግለሰቡ ሊቀወም ወይም ሊያስቆም የሚችለው ይህን ሰፊና አሻሚ ትርጉም ያለውን የተለየ አስተያየት /ለቦሰስቅቋሽቄቃ/ ውሰጥ ካልወደቀ ብቻ ነው፡፡

 ተጨማሪ አስተያየት ወይም ጥያቄ ካለዎት ያግኙን

 

አግባብነት ያላቸው ተጨማሪ ህግ መረጃዎች ከማናቸውም ኢትዮጵያዊ የቤተሰብ ጠበቃ፣ኢትዮጵያዊ የወንጀል ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የንብረት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የካሳ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የንግድ ምልክት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የኢሚግሬሽን ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የፓተንት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የኮፒራይት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የስራ ፈቃድ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ ጠበቃ… ማግኘት ይችላሉ፡፡