አዋጅ ቁጥር 721/2004

የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ

መሬት የመንግስትና የሕዝብ ንብረት ሆኖ የመሬት አጠቃቀም በሕግ እንደሚወሰን በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 40 የተደነገገ በመሆኑ፤

በመላ ሀገሪቱ በሁሉም ክፍላተ-ኢኮኖሚዎችና ክልሎች በመመዝገብ ላይ ያለው ቀጣይነት የተላበሰ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት የከተማ መሬት ፍላጐትን በዘላቂነትና በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ እንዲመጣ በማድረጉና ይህም ሁኔታ  ብቃት በተላበሰና ለፍላጎቱ ተገቢ የመሬት ሀብት አቅርቦት ምላሽ ሊሰጥ በሚችል አስተዳደር በአግባቡ መመራት ያለበት በመሆኑ፤

ለተሳለጠ፣ ለውጤታማ፣ ለፍትሐዊና ለጤናማ የመሬትና መሬት ነክ ንብረት ገበያ ልማት፤ ቀጣይነት ለተላበሰ የነፃ ገበያ ሥርዓት መስፋፋት፣ ግልጽና ተጠያቂነት ለሰፈነበት እንዲሁም የመሬት ባለቤቱንና የመሬት ተጠቃሚውን  መብቶችና ግዴታዎችን ለማረጋገጥ የሚያስችል የመሬት አስተዳደር ሥርዓት ለመገንባት የመልካም አስተዳደር መኖር እጅግ መሠረታዊ ተቋማዊ ፍላጐት በመሆኑ፤

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ 2(ሀ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

ክፍል አንድ

ጠቅላላ

1. አጭር ርዕስ

ይህ አዋጅ “የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ ቁጥር ——-/2003’’ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

2. ትርጓሜ

የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ፤

1/ “ሊዝ” ማለት በጊዜ በተገደበ ውል መሠረት የከተማ ቦታ የመጠቀም መብት የሚገኝበት የመሬት ይዞታ ስሪት ነው፤

2/ “የከተማ ቦታ” ማለት በከተማ አስተዳደራዊ ወሰን ክልል ውስጥ የሚገኝ መሬት ነው፤

3/ “ከተማ” ማለት ማዘጋጃ ቤት የተቋቋመበት ወይም ሁለት ሺህ ወይም ከዚያ በላይ የህዝብ ቁጥር ያለውና ከዚህ ውስጥ 50% የሚሆነው የሰው ኃይል ከግብርና ውጭ በሆነ ሥራ ላይ የተሰማራ ሆኖ የሚገኝበት አካባቢ ነው፤

4/ “ክልል” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 47(1) የተመለከተው ማንኛውም ክልል ነው፤

5/ “የከተማ አስተዳደር” ማለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወይም የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ነው፤

6/ “አግባብ ያለው አካል” ማለት የከተማ ቦታን ለማስተዳደርና ለማልማት ሥልጣን የተሰጠው የክልል ወይም የከተማ አስተዳደር አካል ነው፤

7/ “የሕዝብ ጥቅም” ማለት በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ሕዝቦች በመሬት ላይ ያላቸውን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን በቀጣይነት ለማጎልበት አግባብ ያለው አካል በከተማው ፕላን መሠረት የሕዝብ ጥቅም ብሎ የሚወስነው የመሬት አጠቃቀም ነው፤

8/ “የከተማ ፕላን” ማለት ሥልጣን ባለው አካል የፀደቀና ህጋዊ ተፈፃሚነት ያለው የከተማ መዋቅራዊ ፕላን፣ የአካባቢ ልማት ፕላን ወይም መሠረታዊ ፕላን ሲሆን አባሪ የፅሁፍ ማብራሪያዎችን ይጨምራል፤

9/ “ጨረታ” ማለት የከተማ የመሬት ይዞታ በገበያ የውድድር ሥርዓት በሚወጡ የውድድር መስፈርቶች መሰረት አሸናፊ ለሚሆነው ተጫራች የከተማ መሬት በሊዝ የሚተላለፍበት ስልት ነው፤

10/ “ምደባ” ማለት በጨረታ ሊስተናገዱ ለማይችሉ ተቋማት የከተማ ቦታ በሊዝ የሚፈቀድበት ስልት ነው፤

11/ “የሊዝ መነሻ ዋጋ” ማለት ዋና ዋና የመሰረተ ልማት አውታሮች የመዘርጊያ ወጪን፣ ነባር ግንባታዎች ባሉበት አካባቢ የሚነሱ ግንባታዎችና ንብረቶችን ለማንሳት የሚያስፈልገውን ወጪና ለተነሺዎች የሚከፈል ካሣን እና ሌሎች አግባብ ያላቸው መሥፈርቶችን ታሳቢ ያደረገ የመሬት የሊዝ ዋጋ ነው፤

12/ “የችሮታ ጊዜ” ማለት መሬት በሊዝ የተፈቀደለት ሰው የመሬቱን የሊዝ ቅድመ ክፍያ ከከፈለ በኃላ በየአመቱ መከፈል ያለበትን መክፈል ከመጀመሩ በፊት ከክፍያ ነጻ ሆኖ እንዲቆይ የሚፈቀድለት የእፎይታ ጊዜ ነው፤

13/ “ግንባታ መጀመር” ማለት በቦታው ላይ ለመስራት ከተፈቀደው ግንባታ ወይም ሕንፃ ቢያንስ የመሠረት ሥራ መሥራትና የኮለን ግንባታ ለማከናወን የሚያስችሉ የኮለን ብረቶች የማቆም ሥራ ማጠናቀቅ ነው፤

14/ “የመሠረት ግንባታ ማጠናቀቅ” ማለት በፕላኑ መሰረት የዋናው ግንባታ መሬት ተቆፍሮ ሙሉ በሙሉ አርማታ የተሞላ፣ የወለል ሥራው የተጠናቀቀና የመጀመርያው ወለል ግድግዳ ግንባታው የተጀመረ ማለት ነው፤

15/ “ግንባታን በግማሽ ማጠናቀቅ” ማለት፣

ሀ) ቪላ ሲሆን የመሠረቱን፣ የኮለኖችና ለጣሪያ ውቅር የሚያስፈልጉ ቢሞችን ሥራ ማጠናቀቅ፣

ለ) ፎቅ ሲሆን የመሠረቱንና ከጠቅላላው ወለሎች ውስጥ 50% የሚሆኑትን የሶሌታ ሥራ ማጠናቀቅ፣ ወይም

ሐ) ሪል ስቴት ሲሆን የሁሉንም ብሎኮች ግንባታ እንደአግባቡ በዚህ ንዑስ አንቀጽ ተራ ፊደል (ሀ) ወይም (ለ) በተመለከተው ደረጃ ማጠናቀቅ፣ ነው፤

16/ “ግንባታ ማጠናቀቅ” ማለት በሊዝ የተፈቀደ ቦታ ላይ እንዲገነባ የተፈቀደን ግንባታ በተሰጠው የግንባታ ፈቃድ መሰረት ሙሉ በሙሉ መሥራትና ዋና ዋና አገልግሎቶች ተሟልተውለት ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረግ ነው፤

17/ “ነባር ይዞታ” ማለት የከተማ ቦታ በሊዝ ስርዓት መተዳደር ከመጀመሩ በፊት በሕጋዊ መንገድ የተያዘ ወይም ሊዝ ተግባራዊ ከሆነ በኃላ ለነባር ይዞታ ተነሺ በምትክ የተሰጠ ቦታ ነው፤

18/ “የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ቦታ” ማለት በመሬት አጠቃቀም ፕላን መሰረት ለማንፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ አገልግሎት የተከለለ ወይም የተዘጋጀ ወይም የተሰጠ ቦታ ነው፤

19/ “ግዙፍ ሪል ስቴት” ማለት በከተሞች ውስጥ የሚታየውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ ለሽያጭ ወይም ለኪራይ አገልግሎት የሚውሉ ቢያንስ ከ1,000 ያላነሱ ቤቶችን የሚገነባ የቤቶች ልማት ነው፤

20/ “ልዩ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክቶች” ማለት ለኢትዮጵያ ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ከፍተኛ ለውጥ የሚያመጡ የልማት ፕሮጀክቶች፣ ወይም የትብብር መስኮች ለማስፋት በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ሀገሪቱ ከሌሎች ሀገሮች ጋር ለሚኖራት የተሻለ ግንኙነት መሠረት እንዲጥሉ የታቀዱ ፕሮጀክቶች ናቸው፤

21/ ”ሚኒስቴር” ማለት የከተማ ልማትና የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ነው፤

22/ “ሰው” ማለት ማንኛውም የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፤

23/ ማንኛውም በወንድ ፆታ የተገለፀው አነጋገር ሴትንም ይጨምራል።

ክፍል ሁለት

መሠረታዊ የሊዝ ድንጋጌዎች

3. ጠቅላላ

1/ የከተማ ቦታን የመጠቀም መብት በሊዝ የሚፈቀደው ለህዝቡ የጋራ ጥቅምና ዕድገት እንዲውል ለማድረግ ይሆናል፡፡

2/ የሊዝ ጨረታ አቅርቦትና የመሬት አሰጣጥ ስርዓቱ ግልጽነትና ተጠያቂነትን የተከተለ በማድረግ ሙስናንና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ከአድሎ የጸዳ እንዲሆን መደረግ አለበት፡፡

3/ ጨረታ የመሬትን የወቅቱን የልውውጥ ዋጋ የሚያስገኝ መሆን አለበት::

4/ የከተማ ቦታ አሰጣጥ ስርዓቱ የህዝቡንና የከተሞችን ጥቅም በቀዳሚነት በማስከበር የከተማ ልማትን በማፋጠንና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ የዜጎችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የሀገሪቱን ልማት ቀጣይነት የሚያረጋግጥ መሆን አለበት፡፡

4. ከሊዝ ሥሪት ውጪ ቦታ መያዝና መፍቀድ ስለመከልከሉ

1/ የዚህ አዋጅ አንቀጽ 5 ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ማንኛውም ሰው የከተማ መሬትን በዚህ አዋጅ ከተደነገገው የሊዝ ሥርዓት ውጪ መያዝ አይችልም፡፡

2/ ማንኛውም ሰው አግባብ ካለው አካል ፈቃድ ሳያገኝ በህጋዊነት ከያዘው ይዞታ ጎን ያለን የከተማ ቦታ አስፋፍቶ መከለልና መጠቀም አይችልም፡፡

3/ ማንኛውም ክልል ወይም የከተማ አስተዳደር በዚህ አዋጅ ከተደነገገው ውጪ የከተማ መሬትን መፍቀድ ወይም ማስተላለፍ አይችልም፡፡

4/ የክልሎች ካቢኔዎች ይህ አዋጅ ለተወሰነ ጊዜ ተፈጻሚ ሳይሆን እንዲቆይ የሚደረግባቸውን ከተሞች ሊወስኑ ይችላሉ፡፡ ሆኖም አዋጁ ከጸናበት ቀን ጀምሮ በማንኛውም ከተማ ላይ ተፈጻሚ ሳይደረግ ሊቆይ የሚችልበት የመሸጋገሪያ ጊዜ ከአምስት ዓመት ሊበልጥ አይችልም፡፡

5/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 4 የተመለከቱት ከተሞች በመሸጋገሪያ ጊዜው ውስጥ የከተማ ቦታን ሊሰጡ የሚችሉት በጨረታ ይሆናል፡፡ የጨረታው መነሻ ዋጋም የአካባቢው አመታዊ የቦታ ኪራይ ተመን ይሆናል፡፡

5. ነባር ይዞታዎች ወደ ሊዝ ሥሪት ስለሚቀየሩበት ሁኔታ

1/ ነባር ይዞታዎች ወደሊዝ ሥሪት የሚቀየሩበት ሁኔታ ሚኒስቴሩ በሚያቀርበው ዝርዝር ጥናት ላይ ተመሥርቶ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ይወሰናል። ሆኖም የጥናቱ ሂደት የነባር ኪራይ ተመን መከለስን አይከለክልም፡፡

2/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት ነባር ይዞታዎች ወደሊዝ በሚቀየሩበት ወቅት በአገር አቀፍ ደረጃ ተፈጻሚ እንዲሆን በሚጸድቀው ስታንዳርድና በከተማው ፕላን መሠረት በሚደረግ ሽንሻኖ የሚቀነስ ወይም የሚጨመር የከተማ ቦታ ይዞታ ሲኖር፣

ሀ) ከሚቀነሰው ይዞታ ላይ ለሚነሳ ንብረት አግባብ ባለው ሕግ መሠረት ካሣ ይከፈላል፤ ወይም

ለ) ለሚጨመረው ይዞታ የሚፈጸመው ክፍያ በሊዝ አግባብ ይስተናገዳል፡፡

3/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) ድንጋጌ ቢኖርም በነባር ይዞታ ላይ የሰፈረ ንብረት ባለቤትነት ከውርስ በስተቀር በማናቸውም መንገድ ለሌላ ሰው ከተላለፈ ንብረቱ የተላለፈለት ሰው የቦታው ባለይዞታ ሊሆን የሚችለው በሊዝ ሥሪት መሰረት ይሆናል፡፡

4/ አግባብ ባለው አካል ሳይፈቀድ የተያዙ ይዞታዎችን ሥርዓት ለማስያዝ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የሚያወጧቸውን ደንቦች ተከትሎ ከከተሞች ፕላንና ከሽንሻኖ ስታንዳርድ አንፃር ተቀባይነት የሚያገኙ ይዞታዎች በሊዝ ሥሪት ይተዳደራሉ::

5/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (4) መሰረት በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች የማስተካከሉ ሂደት ተፈፃሚ የሚሆነው ይህ አዋጅ ከሚጸናበት ቀን ጀምሮ ባለው የአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ ብቻ ይሆናል፡፡

6/ ነባር ይዞታና የሊዝ ይዞታ እንዲቀላቀል ጥያቄ ቀርቦ ይዞታው እንዲቀላቀል ከተፈቀደ ጠቅላላ ይዞታው በሊዝ ሥሪት ይተዳደራል፡፡

7/ በዚህ አንቀጽ መሰረት ወደ ሊዝ ሥሪት የሚገቡ ይዞታዎችን በተመለከተ ተፈጻሚ የሚሆነው የሊዝ ክፍያ መጠን በአካባቢው የሊዝ መነሻ ዋጋ መሠረት ይሆናል፡፡

6. የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመፍቀድ

የከተማ ቦታ በሊዝ እንዲያዝ የሚፈቀደው፣

1/ ከተማው ኘላን ያለው ሲሆን የኘላኑን የቦታ አጠቃቀም ድንጋጌ ወይም ከተማው ኘላን የሌለው ሲሆን ክልሉ ወይም የከተማ አስተዳደሩ የሚያወጣውን ደንብ በመከተል፣ እና

2/ በጨረታ ወይም በምደባ ስልት ይሆናል።

7. ለጨረታ ስለሚዘጋጁ የከተማ ቦታዎች

አግባብ ያለው አካል፣

1/ ለጨ[ታ የተዘጋጁ የከተማ ቦታዎች ለሕዝብ ይፋ ከመደረጋቸው በፊት

ሀ) ከማንኛውም የይገባኛል ጥያቄ ነጻ መሆናቸውን፤

ለ) የከተማውን ፕላን ተከትለው የተዘጋጁ መሆናቸውን፤

ሐ) መሠረታዊ የመሠረተ ልማት አውታሮች አቅርቦት ያላቸው መሆኑን፤

መ) ተሸንሽነው የወሰን ድንጋይ የተተከለላቸውና ልዩ የፓርስል መለያ ቁጥር የተሰጣቸው መሆናቸውን፣

ሠ) ሳይት ፕላንና ሌሎች አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች የተዘጋጁላቸው መሆናቸውን፣ እና

2/ የጨረታው አፈጻጸም ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለበት አሠራር የመሬቱን ትክክለኛ ዋጋ በሚያስገኝ መልኩ መከናወኑን፣

ማረጋገጥ ›ለበት፡፡

8. ለጨረታ የተዘጋጀ የከተማ ቦታ መረጃዎች

1/ ለጨረታ የተዘጋጀ የከተማ ቦታን የሚመለከት መረጃ የቦታውን ደረጃ& የሊዝ መነሻ ዋጋና አግባብነት ያላቸው ሌሎች ዝርዝር መረጃዎችን መያዝ አለበት፡፡

2/ ለጨረታ የተዘጋጀ የከተማ ቦታ የተለየ የልማት መርሀ ግብርና የአፈጻጸም ሰሌዳ የሚያስፈልገው ከሆነ የልማት መርሀ ግብሩና የአፈጻጸም ሰሌዳው በመረጃው ውስጥ እንዲካተት ይደረጋል፡፡

9. ለጨረታ የሚቀርቡ የከተማ ቦታዎች ዕቅድን ለህዝብ ይፋ ስለማድረግ

1/ አግባብ ያላቸው አካላት፣

ሀ) የመሬት አቅርቦት ፍላጎትንና ትኩረት የሚደረግባቸውን የልማት መስኮች መሰረት በማድረግ በየዓመቱ ለጨረታ የሚያወጡትን የከተማ ቦታ መጠን በመለየት ዕቅዳቸውን ለህዝብ ይፋ ማድረግ፣ እና

ለ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ 8 የተመለከቱትን መረጃዎች ሕዝቡ በቀላሉ ሊያገኛቸው እንዲችል ማድረግ፣ አለባቸው፡፡

2/ አግባብ ያላቸው አካላት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት ለህዝብ ይፋ ያደረጉትን እቅዳቸውን ተከትለው ወቅቱን የጠበቀ የመሬት አቅርቦት እንዲኖር የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው፡፡

10. የጨረታ ሂደት

1/ አግባብ ያለው አካል የሊዝ ጨረታ ለማካሄድ የጨረታ ማስታወቂያ ማውጣትና የጨረታ ሰነድ መሸጥ አለበት፡፡

2/ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ በቀላሉ በሚያገኙበት አግባብ የሚፈፀም ይሆናል፤ ሆኖም አንድ ተጫራች ለአንድ ቦታ ከአንድ የጨረታ ሰነድ በላይ በመግዛት መወዳደር አይችልም፡፡

3/ የጨረታ ማስከበርያ መጠን በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች በሚወጡ ደንቦች የሚወሰን ሆኖ በማንኛውም ሁኔታ ከመሬቱ የሊዝ መነሻ ዋጋ ከአምስት በመቶ በታች ሊሆን አይችልም፡፡

4/ ለመጀመርያ ጊዜ በወጣ የሊዝ ጨረታ ቢያንስ ሦስት ተወዳዳሪዎች ካልቀረቡ ጨረታው ይሰረዛል፡፡

5/ በአቀረበው የጨረታ ዋጋና የቅድሚያ ክፍያ መጠን ላይ ተመሥርቶ ከፍተኛውን ነጥብ ያገኘ ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ይሆናል፡፡

6/ የጨረታ አሸናፊዎች ዝርዝርና ያገኙት የውድድር ውጤት በማስታወቂያ ሰሌዳ ለህዝብ ይፋ መደረግ አለበት፡፡

7/ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች በግል ለሚካሄዱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋሞች፣ ሆስፒታሎች፣ የጤና ምርምር ተቋማት፣ ባለ አራት ኮከብና ከዚያ በላይ ደረጃ ላላቸው ሆቴሎች እና ግዙፍ ሪል እስቴቶች የሚሆኑ ቦታዎችን በቅድሚያ በማዘጋጀት ቦታዎቹ በጨረታ አግባብ የሚስተናገዱበትን ሁኔታ ያመቻቻሉ::

8/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (4) የተደነገገው ቢኖርም& በጨረታው ለመሳተፍ የቀረበው አንድ ተጫራች ብቻ ቢሆንም ፕሮጀክቱ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (7) ሥር የሚወድቅ ከሆነ የማልማት አቅሙ አግባብ ባለው አካል ተረጋግጦ ይስተናገዳል፡፡

11. በምደባ ስለሚሰጥ የከተማ ቦታ

1/ በሚመለከተው ክልል ወይም የከተማ አስተዳደር ካቢኔ እየተወሰኑ የሚከተሉት የከተማ ቦታዎች በምደባ እንዲያዙ ሊፈቀዱ ይችላሉ፤

ሀ) ለባለበጀት የመንግስት መሥርያ ቤቶች ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎች፤

ለ) በመንግሥት ወይም በበጎ አድራጎት ድርጅቶች ለሚካሄዱ ማህበራዊ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት የሚውሉ ቦታዎች፤

ሐ) በመንግስት ለሚካሄዱ የ¬ጋራ መኖርያ ቤቶች ልማት ፕሮግራሞች እና በመንግስት እየተወሰነ ለሚካሄዱ ለራስ አገዝ የጋራ መኖርያ ቤት ግንባታዎች  የሚውሉ ቦታዎች፤

መ) ለእምነት ተቋማት አምልኮ ማካሄጃ የሚውሉ ቦታዎች፤

ሠ) ለማኑፋክቸሪንግ ኢንደስትሪዎች ልማት የሚውሉ ቦታዎች፤

ረ) ከመንግሥት ጋር በተደረጉ ስምምነቶች ለኤምባሲዎችና ለአለምአቀፍ ድርጅቶች አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎች፤

ሰ) በክልሉ ፕሬዚዳንት ወይም በከተማው አስተዳደር ከንቲባ እየታዩ ለካቢኔው ለሚመሩ ልዩ አገራዊ ፋይዳ ላላቸው ፕሮጀክቶች የሚውሉ ቦታዎች፡፡

2/ በከተማ መልሶ ማልማት ፕሮግራም ምክንያት ተነሺ የሚሆን የነባር ይዞታ ባለመብት ምትክ ቦታ የማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡

3/ በክልል ወይም በድሬደዋ ከተማ የመንግስት ወይም የቀበሌ መኖርያ ቤት ህጋዊ ተከራይ የሆነ ሰው በከተማ መልሶ ማልማት ፕሮግራም ምክንያት ተነሺ በሚሆንበት ጊዜ ተተኪ ቤት የሚያገኝበትን ሁኔታ ማመቻቸት ካልተቻለ የመኖርያ ቤት መስርያ የከተማ ቦታ በሊዝ መነሻ ዋጋ የማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡ ሆኖም አግባብ ያለው አካል የሚወስነውን የአቅም ማሳያ ገንዘብ በዝግ የባንክ ሂሳብ ማስቀመጥ አለበት፡፡

4/ በአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ወይም የቀበሌ መኖርያ ቤት ህጋዊ ተከራይ የሆነ ሰው በከተማው መልሶ ማልማት ፕሮግራም ምክንያት ተነሺ በሚሆንበት ጊዜ የጋራ መኖርያ ቤት በግዥ የሚያገኝበት ሁኔታ ይመቻችለታል፡፡

5/ የመንግስት ወይም የቀበሌ የንግድ ቤት ህጋዊ ተከራይ የሆነ ሰው  በከተማ መልሶ ማልማት ፕሮግራም ምክንያት ተነሺ በሚሆንበት ጊዜ በሚመለከተው ክልል ወይም የከተማ አስተዳደር በሚወሰነው መሠረት ይስተናገዳል፡፡

12. የከተማ ቦታ ምደባ ጥያቄ አቀራረብ

የከተማ ቦታ በምደባ አማካይነት በሊዝ ለመያዝ የሚቀርብ ጥያቄ ከሚከተሉት ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት፤

1/ ጥያቄ ያቀረበው ተቋም የበላይ ተቆጣጣሪ አካል ወይም የዘርፍ አካላት የድጋፍ ደብዳቤ፤

2/ በቦታው ላይ የሚከናወነው ፕሮጀክት ዝርዝር ጥናት፤ እና

3/ ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ የተመደበለት በጀት ማስረጃ::

13. የከተማ ቦታ የሊዝ ዋጋ

1/ ማንኛውም የከተማ ቦታ የሊዝ መነሻ ዋጋ ይኖረዋል፡፡ የመነሻ ዋጋ ትመና ዘዴው በሚመለከታቸው ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች በሚወጡ ደንቦች መሠረት የየከተሞቹን ነባራዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ይወሰናል፡፡

2/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሰረት የተሰላውን የከተማ ቦታዎች የሊዝ መነሻ ዋጋ መሰረት በማድረግ የዋጋ ቀጠና ካርታ መዘጋጀት አለበት፡፡

3/ የሊዝ መነሻ ዋጋ ወቅታዊነቱን ጠብቆ እንዲሄድ ቢያንስ በየሁለት ዓመቱ መከለስ አለበት፡፡

14. የችሮታ ጊዜ

1/ የከተማ ቦታ በሊዝ የተፈቀደለት ሰው እንደ ልማቱ ወይም አገልግሎቱ ዓይነት የችሮታ ጊዜ ሊሰጠው ይችላል፡፡ ዝርዝሩ በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች በሚወጡ ደንቦች ይወሰናል፡፡

2/ የችሮታ ጊዜ የሊዝ ውል ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ ሆኖ በማንኛውም ሁኔታ ከግንባታ ማጠናቀቅያ ጊዜ መብለጥ የለበትም፡፡

ክፍል ሦስት

የከተማ ቦታ ሊዝ አስተዳደር

15. የሊዝ ውል yl!Z ውል መፈራረም ይኖርበታል

1/ በዚህ አዋጅ መሠረት የከተማ ቦታ በሊዝ እንዲይዝ የተፈቀደለት ሰው አግባብ ካለው ጋር የሊዝ ውል መፈራረም ይኖርበታል ውል መፈራረም ይኖርበታል፡፡

2/ የሊዝ ውሉ የግንባታ መጀመርያ፣ የግንባታ ማጠናቀቅያ፣ የክፍያ አፈፃፀም ሁኔታ፣ የችሮታ ጊዜ፣ የውል ሰጪና የውል ተቀባይ መብትና ግዴታዎች እንዲሁም ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ዝርዝር ሁኔታዎች ማካተት አለበት፡፡

3/ የከተማ ቦታ በሊዝ እንዲይዝ የተፈቀደለት ሰው የሊዝ ውል ከመፈረሙ በፊት ስለውሉ ይዘት እንዲያውቅ ተደርጎ በቅድሚያ የሚከፈለውን የገንዘብ መጠን ገቢ የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡

4/ የሊዝ ውል የፈረመ ሰው በዚህ አዋጅ አንቀጽ 16 በተገለፀው መሰረት በስሙ የተዘጋጀ የሊዝ ይዞታ የምስክር ወረቀትና ቦታውን በመስክ ተገኝቶ የሚረከብ ይሆናል፡፡

5/ አግባብ ያለው አካል በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (4) መሰረት ርክክብ የተፈፀመበት የከተማ ቦታ በሊዝ ውሉ መሠረት እንዲለማ መደረጉንና በየዓመቱ የሚከፈለው የሊዝ ክፍያ ወቅቱን ጠብቆ እየተፈጸመ ስለመሆኑ ክትትል የማድረግና የማረጋገጥ ኃላፊነት ይኖርበታል፡፡

16. የሊዝ ይዞታ የምስክር ወረቀት

1/ የከተማ ቦታ በሊዝ የተፈቀደለት ሰው የሊዝ ይዞታ ምስክር ወረቀት ይሰጠዋል፡፡

2/ የሊዝ ይዞታ የምስክር ወረቀት የሚከተሉትን መግለጫዎች አካቶ መያዝ አለበት፤

ሀ) ቦታ በሊዝ የተፈቀደለትን ሰው ሙሉ ስም ከእነአያት፤

ለ) የቦታውን ስፋትና አድራሻ፤

ሐ) የቦታውን የአገልግሎት ዓይነት፣ ደረጃና የፕሎት ቁጥር፤

መ) የቦታውን ጠቅላላ የሊዝ ዋጋና በቅድሚያ የተከፈለውን መጠን፤

ሠ) በየዓመቱ የሚፈጸመውን የሊዝ ክፍያ መጠንና ክፍያው የሚጠናቀቅበትን ጊዜ፤

ረ) የሊዝ ይዞታው ፀንቶ የሚቆይበትን ዘመን፡፡

17. የሊዝ ዘመን

1/ የከተማ ቦታ ሊዝ ዘመን እንደየከተማው የዕድገት ደረጃና የልማት ሥራው ዘርፍ ወይም የአገልግሎቱ ዓይነት ሊለያይ የሚችል ሆኖ ጣሪያው እንደሚከተለው ይሆናል፤

ሀ) በማናቸውም ከተማ፤

(1) ለመኖሪያ ቤት፣ ለሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ ለምርምርና ጥናት፣ ለመንግስት መሥሪያ ቤት፤ ለበጎ አድራጎት ድርጅትና ለሃይማኖት ተቋም 99 ዓመታት፤

(2) ለከተማ ግብርና 15 ዓመታት፤

(3) ለዲኘሎማቲክና ለዓለም አቀፍ ተቋማት በመንግሥት ስምምነት መሠረት ለሚወሰን ዓመት፤

ለ) በአዲስ አበባ ከተማ፤

(1) ለትምህርት፣ ለጤና፣ ለባህልና ለስፖርት 90 ዓመታት፣

(2) ለኢንዱስትሪ 70 ዓመታት፣

(3) ለንግድ 60 ዓመታት፣

(4) ለሌሎች 60 ዓመታት፤

ሐ) በሌሎች ከተሞች፤

(1) ለትምህርት፣ ለጤና፣ ለባህልና ለስፖርት 99 ዓመታት፤

(2) ለኢንዱስትሪ 80 ዓመታት፤

(3) ለንግድ 70 ዓመታት፤

(4) ለሌሎች 70 ዓመታት፡፡

2/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) የተደነገገው ቢኖርም፣

ሀ) በባሕሪው ረዘም ያለ የሊዝ ይዞታ ዘመን ለሚጠይቅ የልማት ሥራ ወይም አገልግሎት ከተወሰነው ዘመን ጣሪያ ከግማሽ ሳይበልጥ ሊጨመር ይችላል፤

ለ) ለጊዜው በልማት ሥራ ጥቅም ላይ በማይውሉ የከተማ ቦታዎች ላይ ለሚቀርቡ የአጭር ጊዜ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተቋማት የቦታ ጥያቄዎች ከአምስት ዓመት ለማይበልጥ ጊዜ በሊዝ ይስተናገዳሉ፡፡ እንደአስፈላጊነቱ ለተመሳሳይ ጊዜ ሊታደስላቸው ይችላል፡፡

18. የሊዝ ዘመን ዕድሳት yl!Z zmN s!Ãb” bwQt$ የሚኖሩትን

1/ የሊዝ ዘመን ሲያበቃ በወቅቱ የሚኖሩትን የቦታውን የሊዝ መነሻ ዋጋና ሌሎች መሥፈርቶች መሠረት በማድረግ ሊታደስ ይችላል። ሆኖም የሊዝ ዘመኑ ሊታደስ በማይችልበት ሁኔታ ለሊዝ ባለይዞታው ካሳ አይከፈልም።

2/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) በተመለከተው መሠረት ባለይዞታው የሊዝ ዘመኑ ሊታደስለት የሚችለው የሊዝ ዘመኑ ሊያበቃ ከ10 እስከ 2 ዓመት እስኪቀረው ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ እድሳት እንዲደረግለት መፈለጉን አግባብ ላለው አካል በጽሑፍ ካመለከተ ብቻ ይሆናል፡፡

3/ አግባብ ያለው አካል ማመልከቻው በቀረበለት በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ውሳኔውን ለአመልካቹ በጽሑፍ ማሳወቅ አለበት፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ውሳኔውን ሳያሳውቅ ቢቀር በእድሳት ጥያቄው እንደተስማማ ተቆጥሮ በወቅቱ በሚኖረው የሊዝ መነሻ ዋጋና ለአገልግሎቱ በሚሰጠው የሊዝ ዘመን መሰረት የሊዝ ውሉ ይታደሳል፡፡

4/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (3) መሠረት መልስ መስጠት የነበረበት የሥራ ኃላፊ ወይም ሠራተኛ በዕድሳቱ ምክንያት የደረሰ ጉዳት ካለ ተጠያቂ ይሆናል፡፡

19. የመክፈያ ጊዜ

1/ የከተማ ቦታ በሊዝ የተፈቀደለት ሰው ወጪውን ለመመለስ የሚያስፈልገውን ጊዜ ግምት ውስጥ በማስገባት የሚወሰን የመክፈያ ጊዜ ሊሰጠው ይችላል፡፡

2/ የቅድሚያ ክፍያ እንደየክልሉና የከተማ አስተዳደሩ ሁኔታ የሚወሰን ሆኖ ከጠቅላላ የቦታው የሊዝ ክፍያ መጠን 10% ማነስ የለበትም፡፡

3/ የቅድሚያ ክፍያው ከተከፈለ በኃላ የሚቀረው የሊዝ ዋጋ በመክፈያ ዘመኑ እኩል ዓመታዊ ክፍያ የሚፈጸም ይሆናል፡፡

4/ በቀሪው ክፍያ ላይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የማበደሪያ የወለድ ተመን መሠረት ወለድ ይከፈላል፡፡ የሚመለከተው አካል የየወቅቱን የማበደርያ ወለድ ተመን ተከታትሎ ወቅታዊ የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡

5/ ወቅቱን ጠብቆ በማይፈጸም ዓመታዊ ክፍያ ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዘገዩ የብድር ክፍያዎች ላይ በሚጥለው የቅጣት ተመን መሠረት መቀጫ ይከፍላል፡፡

6/ የሊዝ ባለይዞታው የሊዝ ክፍያውን ለመክፈል በሚገባው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካልከፈለና የሦስት ዓመት ውዝፍ ካለበት አግባብ ያለው አካል ንብረቱን ይዞ በመሸጥ ለውዝፍ ዕዳው መክፈያ የማዋል ሥልጣን ይኖረዋል፡፡

7/ የዚህ አንቀጽ ከንዑስ አንቀጽ (1) እስከ (5) የተደነገገው በዚህ አዋጅ አንቀጽ 11 ንዑስ አንቀጽ (1) ተራ ፊደል (ሀ) ወይም (መ) መሠረት ለባለበጀት የመንግሥት መሥሪያ ቤት ወይም ለሃይማኖታዊ ተቋም በምደባ በሚሰጥ የከተማ ቦታ ላይ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡ ሆኖም ባለበጀት የመንግሥት መሥሪያ ቤቱ ወይም ሃይማኖታዊ ተቋሙ በምደባ ያገኘውን መሬት ለማስለቀቅ የተከፈለውን ካሣ የሚተካ ክፍያ ይከፍላል፡፡

20. በሊዝ የተያዘ የከተማ ቦታ አጠቃቀም

1/ የከተማ ቦታ ሊዝ ባለይዞታ በሊዝ ውሉ ውስጥ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቦታውን ለተፈቀደለት አገልግሎት ጥቅም ላይ ማዋል አለበት፡፡

2/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) የተደነገገው ቢኖርም የሊዝ ባለይዞታው የቦታውን አጠቃቀም ለመለወጥ አግባብ ላለው አካል ሊያመለክት ይችላል፡፡

3/ አግባብ ያለው ባለሥልጣን የታቀደው የቦታ አጠቃቀም ከከተማው የመሬት አጠቃቀም ፕላን ጋር የማይጋጭ መሆኑን ሲያረጋግጥ ለውጡን ሊፈቅድ ይችላል፡፡

21. ግንባታ ስለመጀመር

1/ ማንኛውም የሊዝ ባለይዞታ በሊዝ ውል በተመለከተው የጊዜ ገደብ መሠረት ግንባታ መጀመር አለበት፡፡

2/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) የተደነገገው ቢኖርም እንደ ግንባታው ውስብስብነት እየታየ ክልሉ ወይም የከተማ አስተዳደሩ በሚያወጣው ደንብ መሠረት የግንባታ መጀመርያ ጊዜው ሊራዘም ይችላል፡፡

3/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (5) እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም የሊዝ ባለይዞታ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) እና (2) መሠረት በተወሰነው የጊዜ ገደብ ውስጥ ግንባታውን ካልጀመረ ቦታውን ከተረከበበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን የሊዝ ክፍያና የጠቅላላውን የሊዝ ዋጋ ሰባት በመቶ መቀጮ እንዲከፍል ተደርጎ ቦታውን አግባብ ያለው አካል መልሶ ይረከባል፡፡

4/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 11 ንዑስ አንቀጽ (3) መሠረት የከተማ ቦታ ይዞታ የተፈቀደለት ሰው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) እና (2) መሠረት በተወሰነው የጊዜ ገደብ ውስጥ ግንባታ ካልጀመረ ለአቅም ማሳያ በዝግ የባንክ ሂሳብ ከተያዘው ገንዘብ ላይ ሦስት በመቶ ተቀጥቶ ቦታውን አግባብ ያለው አካል መልሶ ይረከባል፡፡

5/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 11 ንዑስ አንቀጽ (1) ተራ ፊደል (ሀ)፣ (ለ)፣ (ሐ)፣ (መ) ወይም (ረ) መሠረት ቦታ የተፈቀደለት የሊዝ ባለይዞታ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) እና (2) መሠረት በተወሰነው የጊዜ ገደብ ውስጥ ግንባታ ካልጀመረ የሊዝ ውሉ ተቋርጦ ቦታውን አግባብ ያለው አካል መልሶ ይረከባል፡፡

22. ግንባታ ስለማጠናቀቅ

1/ ማንኛውም የሊዝ ባለይዞታ የዚህን አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (2) እና (3) ድንጋጌዎች ተከትሎ በሊዝ ውሉ ውስጥ በተመለከተው የጊዜ ገደብ መሠረት ግንባታውን ማጠናቀቅ አለበት፡፡

2/ የግንባታ ማጠናቀቅያ የጊዜ ገደብ እንደሚከተለው ይሆናል፤

ሀ) ለአነስተኛ ግንባታ 24 ወራት፤

ለ) ለመካከለኛ ግንባታ 36 ወራት፤

ሐ) ለከፍተኛ ግንባታ 48 ወራት።

3/ የግንባታ ደረጃዎች በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች በሚወጡ ደንቦች ይወሰናሉ፡፡

4/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) የተደነገገው ቢኖርም እንደ ግንባታው ውስብስብነት እየታየ ክልሉ ወይም የከተማ አስተዳደሩ በሚያወጣው ደንብ መሠረት የግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜው ሊራዘም ይችላል፡፡ ሆኖም ለግንባታ ማጠናቀቅያ የሚሰጠው ጠቅላላ ጊዜ በማንኛውም ሁኔታ፣

ሀ) ለአነስተኛ ግንባታ ከሁለት ዓመት ከስድስት ወር፣

ለ) ለመካከለኛ ግንባታ ከአራት ዓመት፣ እና

ሐ) ለከፍተኛ ግንባታ ከአምስት ዓመት፣

መብለጥ አይችልም፡፡

5/ ማንኛውም የሊዝ ባለይዞታ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት በተወሰነው የጊዜ ገደብ ግንባታውን ካላጠናቀቀ አግባብ ያለው አካል የሊዝ ውሉን በማቋረጥ ቦታውን መልሶ መረከብ ይችላል፡፡

6/ የሊዝ ውል የተቋረጠበት ሰው በራሱ ወጪ ከስድስት ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ በቦታው ላይ የሠፈረ ንብረቱን ማንሳት አለበት፡፡ ለዚህም አግባብ ያለው አካል በፅሁፍ ማስጠንቀቅያ መስጠት አለበት፡፡

7/ የሊዝ ባለይዞታው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (6) መሠረት ንብረቱን ካላነሳ አግባብ ያለው አካል፣

ሀ) ጅምር ግንባታው በፕላኑ መሰረት የተገነባ መሆኑን አረጋግጦ ግንባታውን ማጠናቀቅና መ