የማይንቀሳቀስ ንብረትን አስመልክቶ ባለቤትነኝ የሚል ክርክር የማቅረብ መብት የመፋለም መብት ይባላል፡፡ ይህ መብት  በ10 ዓመት ይርጋ እንደሚታገድ ከዚህ በፊት ፍርድ ቤቶች አቋም ነበራቸው፡፡ ይህ አቋም ግን አሁን ተቀይሯል፡፡ ስለሆነም ስለተቀየረው የፍርድ ቤቶች አቋም  እንንገራችሁ፡፡

 

የፌደራል ሰበር ሰሚ ፍርድ ቤት በሰ/መ/ቁ 43600 በዳዊት መስፍንና የመንግስት ቤቶች ኤጄንሲ መካከል በነበረው ሙግት በሰኔ 17, 2ዐዐ2 ዓ.ም. አቋም መሰረት ይዟል፡፡

 

ይህ በዳዊት መስፍንና የመንግስት ቤቶች ኤጄንሲ መካከል በነበረው ሙግት የሰበር ፍ/ቤት የሰጠው ፍርድ ውስጥ ስለአለው ቁም ነገር አጭር ማብራሪያ ነው፡፡ ይህ ማብራሪያ ትችት ወይም የጉዳዮ ማብራሪያ አይደለም፡፡

 

የክርክሩ መሠረታዊ ነገር በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚሰራው ይርጋ ነው፡፡

 

ተቃዋሚ የውል ሕግን በመጥቀስ የአመልካች ክስ በይርጋ ታግዷል የሚል ነው፡፡ የተጠቀሰው ሕግ 1677 በመጥቀስ ለማይንቀሳቀስ ንብረትም ያገለግላል የሚል ነው፡፡ በማይንቀሳቀስ ንብረት ሙግት ላይ ሊፀና የሚችል ይርጋ በመፋለም መብት ላይ አይፀናም፡፡ የመፋለም መብት የዘላለም ነው፡፡ ሰበር በተቻለ መጠን የመፋለም መበትን ሊያብራራ ሞክሯል፡፡ በዚህም መሠረት የተቃዋሚ ወገን ሕጋዊ መሠረት አይቆምም፡፡

 

ተጨማሪ አስተያየት ወይም ጥያቄ ካለዎት ያግኙን

 

አግባብነት ያላቸው ተጨማሪ ህግ መረጃዎች ከማናቸውም ኢትዮጵያዊ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ ታክስ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የቤተሰብ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የወንጀል ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የንብረት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የካሳ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የንግድ ምልክት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የኢሚግሬሽን ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የፓተንት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የኮፒራይት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የስራ ፈቃድ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ ጠበቃ … ማግኘት ይችላሉ፡፡