ልማዳዊ/ባህላዊ ጋብቻ በኢትዩጵያ ተቀባይነት እንዳለው ያውቁ ኖሯል? እንግዲያውስ እንንገርዎት፡፡

ልማዳዊ/ባህላዊ ጋብቻ በኢትዩጵያ ተቀባይነት ያለው ቢሆንም ልማዳዊው ጋብቻ ህጋዊ ውጤት ይኖረው ዘንድ ግን በክፍለ ከተማው የጋብቻና ክብር መዝገብ ምዝገባ ቢሮ ውስጥ መመዝገብ ይኖርበታል፡፡ ባልና ሚስት በልማዳዊ ጋብቻ ከተጋቡ በኋላ ህጋዊ በሆነው የጋብቻና ክብር መዝገብ ላይ በፈለጋቸው ጊዜ ጋብቻቸውን ማስመዝገብ ማስመዝገብ የሚችሉ ቢሆንም በግዜ ማስመዝገቡ ግን ይመከራል፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ ባልና ሚስቱ ለምዝገባ በሚሄዱበት ጊዜ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ እነሱም

1. የባህላዊው/ልማዳዊው ጋብቻ ውል ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ፣

2. በባልም ሆነ በሚስት ወገን የሚመጡ ሁለት ሁለት ምስክሮች፡፡ እነዚህ ምስክሮች የነዋሪነት መታወቂያቸው ዋናውንና አንድ አንድ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፣

3. የባልና ሚሰቱ መታወቂያ ይህ ሲባል መታወቂያቸው ጊዜው ያለፈበት ሳይሆን የታደስ መሆን አለበት፣

4. ባልና ሚስቱ ነዋሪነታቸው ጋብቻው በሚመዘገብበት ክፍለ ከተማ መሆን ያለበት ሲሆን አሊያም ደግሞ ጋብቻቸውን ማስመዝገብ የሚችሉት ባልየው  ወይም ሚስትየው ወይም ከሁለቱ አንዳቸው በሚኖሩበት ክፍለ ከተማ መሆን አለበት፣

5. የባል እንዲሁም የሚስት ፓስፖርት ሳይዝ ሦስት ሦስት ጉርድ ፎቶግራፍ፣

6. ከላይ በተራ ቁጥር ሁለት ላይ የጠቅስናቸው ምስክሮች ግዴታ ጋብቻው ሲፈፀም የነበሩ /የተገኙ/ መሆን አይጠበቅባቸውም፡፡ ማንኛውም እድሜው 18/አስራ ስምንት/ አመት የሞላና ባልና ሚስቱን በደንብ የሚያውቅ እንዲሁም ስለ ጋብቻቸው በደንብ ሊያስረዳ የሚችል ሰው ምስክር መሆን ይችላል፡፡

ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ደንበኛ አገልግሎቱን በአንድ ስዓት ውስጥ ፈፅሞ መመለስ የሚችል ሲሆን ለዚህ አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የሚጠይቀው ክፍያ 50.00 (ሀምሣ ብር) የኢትዩጵያ ብር ብቻ ነው፡፡

ተጨማሪ ጥያቄ አስተያየት ቢኖርዎት ያነጋግሩን ይጠይቁን

ኢሜይል  ፡- fikadu@ethiopianlaw.com

አግባብነት ያላቸው ተጨማሪ ህግ መረጃዎች ከማናቸውም ኢትዮጵያዊ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የፍቺ ጠበቃ፣ኢትዮጵያዊ የቤተሰብ ጠበቃ… ማግኘት ይችላሉ፡፡