የገቢ ግብር ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ የገቢ ግብር አዋጅ 286/1994 የሚያስቀምጣቸውን መረጃዎች ከዚህ እንደሚከተለው እንካፍልዎት፡፡

1.  አንድ ድርጅት ይህንን አዋጅ በመተላለፍ ጥፋት የፈፀመ እንደሆነ ጥፋቱ በተፈፀመ ጊዜ የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ የሆነ ማንኛውም ሠው በድርጅቱ የተፈፀመውን ጥፋት እንደፈፀመ ተቆጥሮ በዚህ አዋጅ የተጣለው ቅጣት ተፈፃሚ ይሆንበታል፡፡

2.  ማናቸውም ድርጅት በዚህ አዋጅ መሠረት ሊከፈል የሚገባውን ወይም አዋጁ እንደግብር የሚቆጥረውን ማናቸውንም ሌላ ክፍያ ገቢ ሣያደርግ የቀረ እንደሆነ ጥፋቱ በተፈፀመበት ጊዜ ወይም ጥፋቱ ከተፈፀመበት ጊዜ አስቀድሞ በነበሩት ስድስት ወራት ውስጥ የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ የነበሩ ሠዎች ከድርጅቱ እና ከሌላው ሠው ጋር በአንድነትና በተናጠል የግብር አሰገቢው ባለስልጣን ለሚፈልገው ግብር እና ሌሎች ክፍያዎች ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡

  • ነገር ግን ጥፋቱ የተፈፀመው ግለሠቡ ሳያውቅ ወይም ሳይስማማበት ከሆነ፣
  • አንድ ነገሮችን በጥንቃቄ የሚያይ ሰው በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ የጥፋቱን መፈጸም ለመከላከል ይወስዳቸዋል ተብሎ የሚገመቱ ጥንቃቄዎችን ተገቢውን ትጋት እና የአሠራር ጥበብ የተሞላበት እርምጃ ግለሠቡ ወስዶ የተገኘ እንደሆነ በተራ ቁጥር 1 እና 2 የተገለፁት ተፈፃሚ አይሆኑበትም፡፡

ተጨማሪ አስተያየት ወይም ጥያቄ ካለዎት ያግኙን

አግባብነት ያላቸው ተጨማሪ ህግ መረጃዎች ከማናቸውም ኢትዮጵያዊ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ ታክስ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የቤተሰብ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የወንጀል ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የንብረት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የካሳ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የንግድ ምልክት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የኢሚግሬሽን ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የፓተንት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የኮፒራይት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የስራ ፈቃድ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ ጠበቃ … ማግኘት ይችላሉ፡፡