የገቢ ግብር ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ የገቢ ግብር አዋጅ 286/1994 የሚያስቀምጣቸውን መረጃዎች ከዚህ እንደሚከተለው እንካፍልዎት፡፡ በዚህ አዋጅ መሠረት ከተከፋይ ሂሣብ ላይ ግብር ቀንሶ ገቢ የማድረግ ግዴታ ያለበት ሠው ቀንሶ ገቢ ያላደረገውን የግብር መጠን ለግብር አሰገቢው ባለስልጣን ገቢ የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ አይነት የከፈለውን ሂሣብ ከግብር ከፋዩ መልሶ የማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡ ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ግብር ቀንሶ የማስቀረት ሀላፊነት ያለበት ሠው በዚህ አዋጅ መሠረት ማንኛውም ግብር ከፋይ ያለበት ሀላፊነት ይኖርበታል፡፡ በመሆኑም ገቢ እንዲያደርግ የተጠየቀውን የግብር መጠን የመቃወም ወይም ቀደም ሲል የከፈለው ታክስ እንዲመለስለት የመጠየቅ መብት አለው፡፡

በዚህ አዋጅ በተደነገገው መሰረት ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ግብር ቀንሶ ገቢ ያላደረገ ሰው ከላይ ከተደነገገው በተጨማሪ ለእያንዳንዱ ተገቢውን ግብር ቀንሶ ገቢ ሳያደርግ ለፈጸመው ክፍያ ብር 1000.00 ሺህ መቀጫ ይከፍላል፡፡

ከላይ ከተዘረዘሩት መቀጫዎች በተጨማሪ የሚከተሉት ግለሠቦች ከዚህ በታች የተወሠነውን መቀጫ እንዲከፍሉ ይደረጋል፡፡

ሀ. ከላይ እንደተጠቀሠው ከተከፋይ ሂሣብ ላይ ግብር ቀንሶ ገቢ ያለመደረጉን ያወቀ

ወይም ማወቅ ያለበት ሥራ እሰኪያጅ፣

ለ.  ከተከፋይ ሂሣብ ላይ ግብር ቀንሶ ገቢ ያለመደረጉን ያወቀ ወይም ማወቅ የነበረበት እና ከተከፋይ ሂሣብ ላይ ግብር ቀንሶ ገቢ የማድረጉን ሥርዓት የመከታተል ወይም የመቆጣጠር ሀላፊነት ያለበት ሆኖ ክትትሉን ወይም ቁጥጥሩን በተገቢው መንግድ ባለማከናወኑ ግብሩ ተቀንሶ ገቢ ላለመደረጉ ምክንያት የሆነ የሂሣብ ሀላፊ ወይም ማንኛውም ሌላ ኀላፊ ብር 1ዐዐዐ መቀጫ ይከፍላሉ፡፡

ተጨማሪ አስተያየት ወይም ጥያቄ ካለዎት ያግኙን

አግባብነት ያላቸው ተጨማሪ ህግ መረጃዎች ከማናቸውም ኢትዮጵያዊ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ ታክስ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የቤተሰብ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የወንጀል ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የንብረት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የካሳ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የንግድ ምልክት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የኢሚግሬሽን ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የፓተንት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የኮፒራይት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የስራ ፈቃድ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ ጠበቃ … ማግኘት ይችላሉ፡፡