የገቢ ግብር ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ የገቢ ግብር አዋጅ 286/1994 የሚያስቀምጣቸውን መረጃዎች ከዚህ እንደሚከተለው እንካፍልዎት፡፡

1.  ማንኛውም ግብር ከፋይ ለአንድ የተወሠነ የግብር ዘመን መያዝ የሚገባውን ተገቢ የሂሣብ ሠነድ፣ የሂሣብ መዝገብ እና መግለጫ ያልያዘ እንደሆነ የተወሰነበትን ግብር አስር በመቶ መቀጫ ይከፍላል፡፡

2.  የግብር አሰገቢው ባለሥልጣን ግብር ከፋዩ ተገቢውን የሂሣብ መዝገብ፣ ሠነድ እና ሌሎችንም መረጃዎች ለሁለት ተከታታይ አመታት ሳይዝ የቀረ መሆኑን ሲደርስበት

  1. የግብር አስገቢው ባለሥልጣን ይህንኑ የሚገልፅ ማስታወቂያ ሲልክለት ፈቃድ ሠጨው መ/ቤት የግብር ከፋዩን የንግድ ሥራ ፈቃድ ወደያውኑ ያግዳል፡፡
  2. ግብር ከፋዩ ተገቢውን የሂሣብ መዝገብ ሠነድ እና ሌሎችንም መረጃዎች በ3 ኛው አመትም ያላቀረበ እንደሆነ ይህንኑ የሚገልፅ ማስታወቂያ ሲደርሠው ፈቃድ ሠጪው መ/ቤት የግብር ከፋዩን የንግድ ሥራ ፈቃድ ይሠርዛል፡፡
  3. የግብር አስገቢው ባለሥልጣን ግብር ከፋዩ መዝገብ የመያዝ ግዴታውን ያልተወጣ መሆኑን ሲደርስበት ከዚህ በላይ በተደነገገው መሠረት የግብር ከፋዩ የንግድ ስራ ፈቃድ እንዲታገድ ወይም እንዲሰረዝ ለፈቃድ ሰጪው ባለስልጣን የሚልከው ማስታወቂያ በዚህ አዋጅ መሰረት እንደተሠጠ የግብር ውሣኔ ማስታወቂያ ሆኖ ይቆጠራል፡፡ ስለሆነም የግብር አስገቢው ባለስልጣን ግብር ከፋዩ ግዴታውን ያልተወጣ ለመሆኑ የመጨረሻ ማረጋገጫ ከማግኘቱ በፊት ማስተወቂያውን መላክ የለበትም፡፡

ተጨማሪ አስተያየት ወይም ጥያቄ ካለዎት ያግኙን

አግባብነት ያላቸው ተጨማሪ ህግ መረጃዎች ከማናቸውም ኢትዮጵያዊ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ ታክስ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የቤተሰብ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የወንጀል ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የንብረት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የካሳ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የንግድ ምልክት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የኢሚግሬሽን ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የፓተንት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የኮፒራይት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የስራ ፈቃድ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ ጠበቃ … ማግኘት ይችላሉ፡፡