የገቢ ግብር ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ የገቢ ግብር አዋጅ 286/1994 የሚያስቀምጣቸውን መረጃዎች ከዚህ እንደሚከተለው እንካፍልዎት፡፡ በግብር ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች የወንጀለኛ መቀጫ ህጉን በመተላለፍ የሚፈፀሙ በመሆኑ ክሡ የሚመሠረተው፣ የሚታየው እና ይግባኝ የሚቀርበው በወንጀለኛ መቀጫ ህግ ሥነ-ሥርዓት ይሆናል፡፡

በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ላይ ስለሚፈፀም ጥፋት

ማንኛውም ግብር ከፋይ ከአንድ የበለጠ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ይዞ የተገኘ እንደሆነ በያዘው በእያንዳንዱ ተጨማሪ መለያ ቁጥር ልክ ብር 2ዐ,000.00 በማያንስና ከብር 5ዐ,000.00 በማይበልጥ የገንዘብ መቀጫ እና በእያንዳንዱ ተጨማሪ መለያ ቁጥር ልክ በአምስት አመት እስራት ይቀጣል፡፡

ህግን በመጣስ ግብር ስላለመክፍል

ማንኛውም ግብር ከፋይ ህግን በመጣስ ገቢውን ያላስታወቀ ወይም የሚፈለግበትን ግብር ያልከፈለ እንደሆነ ወንጀል እንደፈፀመ ይቆጠራል፡፡ ስለሆነም በዚህ አዋጅ አንቀፅ 86 መሠረት ገቢውን አሣንሶ በማስታወቁ መክንያት ከሚጣልበት መቀጫ በተጨማሪ ጥፋተኛ መሆኑ በፍርድ ቤት ሲረጋገጥ ከ5 አመት በማያንስ እስራት እንደሚቀጣ የአዋጁ አንቀፅ 96 ይደነግጋል፡፡

የሀሰት ወይም አሣሣች መረጃ ስለማቅረብ

1. ማንኛውም ግብር ከፋይ

  • ለግብር አሰገቢው ባለስልጣን ሠራተኛ አንድን ነጥብ በተመለከተ የሀሠት ወይም አሣሣች መረጃ ያቀረበ ወይም፣
  • ለግብር አስገቢው ባለስልጣን ሠራተኛ ሊቀርብ ከሚገባው መግለጫ ውስጥ መግለጫውን አሣሣች ሊያደርግ በሚችል አኳኋን መካተት የሚገባቸውን ነጥቦች ያስቀረ እንደሆነ የወንጀል ክስ ይመሠረትበታል፡፡

2. የሀሠት መግለጫው የተሠጠው ወይም መካተት የሚገባው ነጥብ የተተወው ያለበቂ ምክንያት የሆነ እንደሆነ

  • የመግለጫው ትክክለኛ ያለመሆን ሊደረስበት ያለመቻሉ ሊከፈል የሚገባው ግብር ከብር 1ዐዐዐ በማይበልጥ አንሶ እንዲከፈል የሚያደርግ ከሆነ ግብር ከፋዩ ከብር 2ዐ.ዐዐዐ ሺ በማይበልጥ የገንዘብ መቀጫ እና ከአንድ አመት በማያንስ እና ከZስት አመት በማይበልጥ እስራት ይቀጣል፡፡
  • አንሶ እንዲከፈል የሚደረገው ግብር ከብር 1 ሺህ የሚበልጥ ከሆነ ከብር 2ዐ.ዐዐዐ በማያንስ አና ከብር 1ዐዐ.000 በማይበልጥ የገንዘብ መቀጫ እና ከZስት አመት በማያንስ እና ከአምስት አመት በማይበልጥ እስራት ይቀጣል፡፡

1.  የሀሠት መግለጫ የተሠጠው ወይም መካተት የሚገባው ነጥብ እንዲካተት ያልተደረገው ሆን ተብሎ ወይም በከባድ ችልተኝነት የሆነ እንደሆነ፡፡

  • የመግለጫው ትክክለኛ ያለመሆን ሊደረስበት ያለመቻሉ ሊከፈል የሚገባው ግብር ከብር 1000.00 በማይበልጥ አንሶ እንዲከፈል የሚያደርግ ከሆነ ግብር ከፋዩ ከብር 50,000.00 ሺህ በማያንስ እና ከብር 100.000.00 ሺህ በማይበልጥ የገንዘብ መቀጫ እና ከአምስት አመት በማያንስ እና ከአስር አመት በማይበልጥ እስራት ይቀጣል፡፡
  • አንሶ እንዲከፈል የሚደረገው ግብር ከብር 1ዐዐዐ.00 የሚበልጥ ከሆነ ከብር 75.ዐዐዐ.00 ሺህ በማያንስ አና ከብር 2ዐዐ.ዐዐዐ.00 ሺህ በማይበልጥ የገንዘብ መቀጫ እና ከ1ዐ አመት በማያንስ እና ከ15 አመት በማይበልጥ አስራት ይቀጣል፡፡

ተጨማሪ አስተያየት ወይም ጥያቄ ካለዎት ያግኙን

አግባብነት ያላቸው ተጨማሪ ህግ መረጃዎች ከማናቸውም ኢትዮጵያዊ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ ታክስ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የቤተሰብ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የወንጀል ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የንብረት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የካሳ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የንግድ ምልክት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የኢሚግሬሽን ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የፓተንት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የኮፒራይት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የስራ ፈቃድ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ ጠበቃ … ማግኘት ይችላሉ፡፡